የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች ዉስጥ እንደሚሰጥ ተገለፀ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እንዳሉት ፈተናው በዩኒቨርስቲ እንዲሰጥ የተወሰነው የፈተና ሰርቆትና ማጭበርበርን ለማስቀረት ታስቦ ነው።
ሚንስትሩ በወርቤ እና ወልቂጤ ከተሞች ተገኝተው በትምህርት ቤቶች ጉብኝት አድርገዋል።
ፈተናው በኤሌክትሮኒክስ /online/ መስጠት እስከሚጀመር ድረስ በዩኒቨርስቲዎች መሰጠቱ ይቀጥላል።
ተማሪዎች ትምህርት በስራና በታታሪነት የሚገኝ መሆኑን አውቀው በርትተው መማር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርትን ጥራትን ለማሻሻል የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ መሆኑን ኃላፊው መናገራቸውን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል።
በሳምሶን ገድሉ
2022-06-29
