ሀገሬ ቲቪ

የወርቅ ሳንቲም መፍትሄ ያቀረበችው ዚምባቡዌ

ዚምባቡዌ በሃገሪቱ ኢንቨስተሮች ሀብታቸውን እንዲያስቀምጡ የሚያስችል የወርቅ ሳንቲም ልታዘጋጅ መሆኑን አስታወቀች። ሀገሪቱ የወርቅ ሳንቲም ልታዘጋጅ መሆኑን የገለጸችው የዚምባቡዌ መገበያያ ገንዘብ ከሌሎች አለም አቀፍ የመገበያያ ገንዘቦች አንጻር ዋጋው ማሽቆልቆሉ ጋር ተያያዞ ነው።

በዚህም የተነሳ በሃገሪቱ የዋጋ ግሽበት በከፍተኛ ሁኔታ አሻቅቧል። የዋጋ ግሽበቱ ከ191 ነጥብ 6 በመቶ ወደ 132 በመቶ ከፍ ማለቱ ተሰምቷል። በወርቅ ሳንቲም ማስተዋወቁ ኢንቨስተሮች ደስተኛ መሆናቸውም ተገልጿል።

በአብርሃም በለጠ
2022-06-29