የዓለምን ረሃብን ለመዋጋት የቡድን 7 አባል ሀገራት 4.5 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ቢገቡም፤አስፈላጊውን እርምጃ አልወሰዱም በሚል ወቀሳ ቀርቦባቸዋል።
በኦክስፋም የእኩልነት አለመኖር ፖሊሲ ኃላፊ የሆኑት ማክስ ሎሰን “በአንድ ትውልድ ውስጥ እጅግ አስከፊ የሆነ የረሃብ ቀውስ ሲገጥም ቡድኑ አስፈላጊውን እርምጃ ባለመውሰዱ ምክንያት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከባድ ረሃብ አጋጥሟቸዋል” ብለዋል።
በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት የምግብ ዋጋ እየጨመረ መምጣት ረሃብና የምግብ ደህንነት ስጋት በተመለከተ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም መፍትሔ አለመገኘቱ ተገልጾል።
በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-06-29
