ሀገሬ ቲቪ

ተአምር የሆነ እሳት የሚያሰቃያት መንደር

እሳት...

ለበርካታ ነገሮች እንጠቀምበታለን። በዛው ልክም ሲያጠፋም እናውቀዋለን። የእሳትን ባህሪ ስናውቀው በአግባቡ እና በጥንቃቄ ካልተጠቀምንበት ያገኘውን ሁሉ የሚያጠፋ ባለ ኃያል ጉልበት ነው። መቼም እኛ ከምንለው በላይ እርሶ የበለጠ ሊረዱት ይችላሉ። ኃያሉ ጉልበተኛው እሳት እመረጠ ያጠፋል ሲባል ሰማን እና ልናጋራችሁ ወደድን።

ካኔቶ ዲ ካሮኒያ በጣልያን ያለች አንዲት መንደር ነች። ታዲያ የዚህች መንደር ነዋዎች ምክንያቱን በማያውቁት ነገር እሳት እየመረጠ ያሰቃያቸው ከገባ ሰነባብቷል። ከ 10 ለበለጡ ዓመታት የዚህች መንደር ነዋዎች መርጦ ቢሚፈጃችው እሳት እየተፈተኑ ይገኛል።

በመንደሩ ሚስጥራዊ የሆነው እሳት ሲያሻው የነዋዎቹን አልጋ፣ አንዳንዴም ፍራሽ፣ መኪናቸውን እንደ ፍሪጅ፣ ስልክ እና ቴሌቪዥኖቻቸውን ብቻ ያነድባቸዋል።

ታዲያ ይህ ቦታ ለበርካታ ዓመታት የጂኦሎጂስቶችን፣ የፊዚክስ ሊቃውንትን እና የእሳተ ገሞራ ባለሙያዎችን ቀልብ ቀልብ ገዝቶ ከርሟል።

እኚህ ሁሉ ሊቃውንት ግን እስካሁን ድረስ የዚህን እሳት ትክክለኛ መነሻ ሳይንሳዊ ማብራሪያ ሊሰጡ አልቻሉም። የመንደሯ ነዋሪዎች ለእዚህ እሳት የማይታወቁትን የማይታወቁ በራሪ አካላት (UFOs)ችን እና የሞቱ ሰዎች መንፈስ አልያም የእርኩሳን መናፍስትን ስራ ነው ባዮች ናቸው።

ይህ ሁሉ የጀመረው ታዲያ በ1996 ዓ.ም ነው። በግዜው በርካታ ቤቶች ውስጥ የነበሩ የቤት እቃዎች በአንዴ ነደዱ። የምግብ ማብሰያ ኦቭኖች እና የቤት ማፅጃ ቫኪውሞችም አልቀሩም፤ ሁሉም የዚህ እሳት ሰለባ ሆኑ። ነዋሪዎቹ በስጦታ ያገኟቸው ስጦታዎች በአንዴ ወደ አመድነት ተቀየሩ።

በግዜው ለአካባቢው የሚደርሰው ኤሌክትሪክ እንዲቋረጥ ቢደረግም የእሳቱ መነሻ እሱ አይደለም እና ለውጥ ሊያመጣ አልቻለም። የሀገሬው መንግስት ወደመንደሯ ወዲያው በቦታው ላይ ምርመራ ለማድረግ ባለሙያዎችን አሰማራ።

ከጣሊያን የባህር ኃይል የተውጣጡ ባለሙያዎች፣ የእሳተ ገሞራ ተመራማሪዎች እና ከብሄራዊ የጂኦፊዚክስ ተቋም ወደስፍራው ያቀኑት ባለሙያዎች ኝ አንዲትም ፍንጭ ማግኘት አልቻሉም።

ታዲያ በዚህ መንደር እሳት አሁንም ይነሳል። የሦስት ቤቶች መስታወቶች 35 ግዜ በተመሳሳይ ሰዓት በእሳት ተያይዘዋል። መንደሯን እሳት ብቻም አይደል ቁም ስቅሏን የሚያሳያት።

በመንደሯ ወስጥ በየቤቱ ያሉ የአየር መቆጣጠሪያ ኤር ኮንዲሽነሮች ሁኔታወን እንዳሻቸው ይለዋውጣሉ፣ በየኮምፒውተሮች ያሉ ሀርድ ድራይቮች የያዙትን ፋይል እንዳለ አጥፍተው ባዷቸውን ይገኛሉ፣ አውቶማቲክ በሮች በራሳቸው ይከፈታሉ ደስ ካላቸው ደግሞ ይዘጋሉ።

ብቻ መንደሯ የማታየው አበሳ የለም። ነዋሪዎቿም መንደራቸውን ለቀው ወደሌላ ስፍራ እንዲሰፍሩ ተደርገዋል። አሁን መንደሯ ባዶዋን ቀርታለች።

በ1997 ዓ.ም የጣሊያን መንግስት በስፍራው ላይ ጥናት የሚያደርግ ቡድን እንዲዋቀር ቢያደርግም ዛሬም ድረስ ግን በመንደሯ የተፈጠረውን ሊያውቅ የሚችል ጠፍቶ ምስጢር እንደሆነ ዘመናትን ተሻግሯል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-06-30