በምንኖርበት ስርዓተ ጸሃይ ውስጥ በርከት ያሉ አስትሮይድ ወይም ግዙፍ አለታማ ድንጋዮች በዋናነት ይገኛሉ።
እነዚህ ዓለታማ ድንጋዮች በመጠን ትናንሽ ፕላኔቶችን የማከል ዕድል እንዳላቸው ይነገራል።
በመሆኑም ዓለታማ ድንጋዮች ወደ ፕላኔቶች በተጠጉ ቁጥር በፕላቶ የስበት ሃይል የመሳብና ከፕላኔቶች ጋር የመላተም እድል እንዳላቸው ይገልጻል።
በጎርጎሮሳውያኑ በታህሳስ 2016 የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ሰኔ 30ን የዓለም አቀፍ የአስትሮይድ ቀን ሲል ሰይሞት እናገኘዋለን።
ዓላማውም የአስትሮይድን አሳሳቢነት ለህብረተሰቡ ለማሳወቅ እንደሆነ ይታወቃል።
እኛም ይህን ቀን በማስመልከት ዶ/ር ሻምበል ሰራው አካሉ በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲቲዩት የስነ ፈለክ ተመራማሪን ጠይቀናል።
እነዚህ አስትሮይዶች መሬትን ከሚያስፈሯት ነግሮች የሚጠቀሱ እንደሆኑ ዶ/ር ሻምበል ነግረውናል።
እንደ ተመራማሪው በተለምዶ ተወርዋሪ ኮከብ የምንላቸው ወደ መሬት ከባቢ አየር በሚገቡበት ወቅት የሚፈጠሩ ብርሃን ናቸው እንጂ ኮከብ እንዳልሆኑ ያስረዳሉ።
በተለያየ ባህል ተወርዋሪ ኮከብ ከተለያየ ዕድል ጋር አብሮ ሲነሳ እንሰማለን ። አሁንም የተለያዩ ሰዎች ተወረዋሪ ኮከብን እንደ ጥሩ ዕድል ይመለከቱታል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-06-30
