ሀገሬ ቲቪ

ከሩሲያ ለፊንላንድና ስዊድን የተላከ ማሳሰቢያ

በዚኽ ሳምንት አብዛኛዎቹ የውጪ ብዙኃን መገናኛዎች የዘገቡት ጉዳይ ነው። የፊንላንድ እና የስዊድን በይፋ የኔቶ አባል ሀገር መኾን። ከዚኽ ጉዳይ ጎን ኔቶን በአይነቁራኛ የምትከታተለው ሩሲያ ምንትል ይኾን የሚለው ደግሞ ተጠባቂ ነበር።

እንደተጠበቀውም የሩሲያ ፕሬዝዳንት በነገሩ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ከፊንላንድ ኾነ ከስዊድን ጋር ምንም ዓይነት ቅሬታም እና ተቃውሞ የለንም ሲሊ ፑቲን ተናግረዋል። ኔቶን መቀላቀላቸውም መብታቸው ነው ይቀጥሉበትም ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ ይኽን አውንታዊ አስተያየት ሰጥተው ብቻ ዝም አላሉም ቀጥለው ማሳሰቢያ የታከለበት አስተያየታቸውን ቀጠሉ እንጂ።

አንዳች ወታደራዊ ማስፈራራት አሊያም በሀገራቱ ወታደራዊ ሰፈራዎች የሚካሔዱ ከኾነ እና ለቀጠናው ሥጋት ፈጣሪ ድርጊቶችን ምታከናወኑ ከኾነ ግን እጃችንን አጣጥፈን አናያችኹም ያናንተን መሰል አቻ ምላሽ እንሰጣለን ብለዋል።

ሞስኮ ከሄልሲንኪ እና ስቶኮልም ጋር ከኔቶ አባልነታቸው ላይ ተያይዞ የገባችበትን ውጥረት ማስወገድ አልችልም ብለዋል ፕሬዝዳንት ፑቲን።

በፊት ላይ ከሀገራቱ ጋር መልካም ዝምድና ነበር አኹን ላይ ዝምድናው ቀዝቅዛ ውኃ ተቸልሶበታል ሲሉ ከኹለቱ ሀገራት ጋር ውጥረት ውስጥ ስለመግባታቸው አብራርተዋል።

ኔቶ የስዊድን እና የፊንላንድን ማመልከቻ ረቡዕ ዕለት በጋራ ውሳኔ አጽድቋል። ይህም ሩሲያ በሀገራቱ ላይ ከንፈር እንድተነክስ አድርጓል።

ኔቶ ቀዝቃዛው ጦርነት በተባለው ጊዜ በ 12 ሀገራት የተቋቋመ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ጥምረት ነው። ዋና ዓላማው የአባል ሀገራቱን ደኀንነት ማስጠበቅ ነው። ከኔቶ አባል ሀገራት አንዳቸው የድኀንነት ስጋት ከገባቸው አሊያም ጦርነት ከገጠሙ ሌሎች አባላት ትብብር ያደርጋሉ።

ሩሲያ ታዲያ ይኽን ትብብር በጽኑ ትኩረት ሰጥታ ትመለከተዋለች በኹለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ሶቪየት ኀብረት ጦሯን ከምስራቅ አውሮፓ ለማስወጣት ፍቃደኛ አልኾንም ባለችበት እና ወደ ጀርመን በርሊን መዞር በጀመረችበት ወቅት ይኽን መስፋፋቷን ለማሰናከል አሜሪካ ኔቶን ኀብረትእንዲቋቋም መሠረት ኾነች።

ከዚያ የጀመረው የኔቶ እንቅስቃሴ አኹን ላይ አባል ሀገራቱ 30 ደርሰዋል። “በአንዱ አባል ሀገር ላይ የሚፈፀም ጥቃት በሁሉም አባል ሀገራት ላይ እንደተፈጸመ ይቆጠራል” በሚለው ድንጋጌ መሠረት አባል ሀገራቱ የጠነከረ ተዛምዶ አላቸው።

የሩሲያ ክፋይ የነበረችው እና አኹን ላይ በጦርነት የምትገኘው ዩክሬንም እጅግ የኔቶ አባል ለመኾን የጠነከረ ጥረት ስታደርግ ቆይታለች።

ሩሲያ ታዲያ ሩሲያ ሙቼ ነው ቆሜ የኔቶ አባል የምትኾኚው ስትል ዩክሬን ስታስፈራራ ነበር። የሩሲያ ዛቻ እንዲኹ አይደለም ምናለባት ዩክሬን ከኔቶ ጋር ብትቀላቀል የኔቶ ብሔራት ኃይሎች በድንበር ላይ ሊሰፍሩ ይችላሉ በዚኽም የኃይል ለውጥ ሊመጣ ስለሚችል ነው።

ምን አልባትም ዩክሬን እንዳሰበችው ቢሳካላት እና የኔቶ አባል ሀገር ብትኾን አኹን ከሩሲያ ጋር የገባችበት ጦርነት የተለየ አውድ ሊኖረው እንደሚችል ይነገራል።

ከሳምንታት በፊት የኢራን ፕሬዝደንት ኢብራሒም ራኢሲ እና የሩሲያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጊዮ ላቭሮቭ ውይይት ካደረጉበት ጉዳይ ኔቶን የተመለከተ ነበር ፕሬዝደንት ኢብራሒም ራኢሲ ኔቶ አባል ሀገራቱን እየጨመረ ዓለምን ለመቆጣጠር የሚሔድበን መንገድ አጥብቀው ተችተዋል ።

በሙሉጌታ በላይ
2022-06-30