የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን በአፋር፣ መተሃራ፣ በሞጆ፣ በአዳማና በተለያዩ ከተሞች ተደብቀው የተገኙት ቦቴዎች ዛሬ እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ነዳጅ ማደያ ካላደረሱ እርምጃ ይወሰዳል አለ።
ከጂቡቲ ተነስተው አዲስ አበባና የተለያዩ ዋና ከተሞች መድረስ የነበረባቸው 200 ነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች ከአዲስ አበባ ውጪ በየሠፈሩ ተደብቀው መገኘታቸውን ጠቁሟል። ከሰሞኑነ የተከሰተው የነዳጅ እጥረትም ሰው ሰራሽ መሆኑን ገልጿል።
በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-06-30
