
ግብፅ ለስንዴ ግዥ ከዓለም ባንክ 500 ሚሊዮን ዶላር ብድር ልታገኝ ነው።
ብድሩ ሀገሪቷ ድሃ ለሆኑና ለአደጋ ለተጋለጡ ቤተሰቦች የዳቦ ድጎማ ለማቅረብ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ያለመ ነው። ግብፅ የዓለማችን ትልቁ የስንዴ አስመጪ ናት፤ ወደ 70 ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ግብጻውያን የሚተማመኑት መንግሥት በሚደግፈው ዳቦ ሲሆን በአብዛኛው የሚጋገረው ከውጭ ከሚመጣ ስንዴ ነው።
ከ103 ሚሊዮን በላይ ከሚሆነው የግብፅ ሕዝብ መካከል አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት በድህነት እንደሚኖሩ መንግሥታዊ አኃዛዊ መረጃዎች ያሳያሉ።
በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-06-30