ሀገሬ ቲቪ

የኤሌክትሪክ ታሪፍ የቀነሰችው ኬኒያ

የኬኒያው መንግሥት የኢንደስትሪ እድገትን ለማበረታታት የኤሌክትሪክ ታሪፍ ክፍያን 30 በመቶ ቀንሻለሁ አለ፡፡ የታሪፍ ቅነሳው ዋና ዓላማ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን የዋጋ ንረት ለማርገብ እና የሀገር በቀል የማኑፋክቸሪንግ እድገትን ለማነቃቃት መሆኑን ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እሁድ እለት በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በተከበረው የነፃነት ቀን ላይ ተናግረዋል፡ ፕሬዝዳንቱ በጥቅምት ወር ሸማቾችን እና የኢንዱስትሪ ተዋንያኖችን ከፍተኛ ወጪ ከሚጠይቁ የኤሌክትሪክ ክፍያዎች ለመጠበቅ በገቡት ቃል መሰረት ነው የኤሌክትሪክ ኃይል ክፍያ ቅናሽ የተደረገው፡፡ በተመሳሳይ ለመኖሪያና ለንግድ ቤቶች የሚቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዋጋ የሚቀንስበትን የማሻሻያ ዘዴ ለመስራት የኢነርጂ ሚኒስቴር ከገለልተኛ ኃይል አምራቾች ጋር ድርድር መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ ይህ የኤሌክትሪክ ኃይል ክፍያ ቅናሽ በ 2022 የመጀመሪያ ሩብ ውስጥ የሚጠናቀቅ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-13