ሀገሬ ቲቪ

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ክስ

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዩናይትድ ስቴትስ ካፒቶል ላይ የተፈጸመው ጥቃት ላይ እጃቸው አለበት በሚል ክስ መቅረቡ አይዘነጋም።

በዚህ ላይ ዘ አሶሺዬትድ ፕሬስ-ኖርሲ የሕዝብ ጉዳይ ምርምር ማዕከል ያደረገው ጥናት እንዳመለከተው 48 በመቶ የሚሆኑት የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች የቀድሞው ፕሬዚዳንት ትራምፕ በወንጀል መከሰስ አለባቸው ይላሉ።

31 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ መከሰስ የለባቸውም እንዲሁም 20 በመቶዎቹ ደግሞ አስተያየት ለመስጠት በቂ እውቀት የለንም ብለዋል። የክስ ሂደቱ አሁንም እንደቀጠለ ነው።

በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-06-30