ሀገሬ ቲቪ

የድጋፍ ሰጪ አዉቶብሶች አገልግሎት አቋረጡ

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ 200 አዉቶብሶች የድጋፍ ሰጭነት ዉላቸዉን በራሳቸው ፈቃድ አቋረጡ አለ። የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶች ውል ለተጨማሪ 6 ወራት የተራዘመ ቢሆንም ውሉን የፈረሙ ግን 180ዎቹ ብቻ ናቸው።

የከተማ አስተዳደሩ ከጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ 380 የሚሆኑ ሀገር አቋራጭ አውቶብሶች በኪራይ መልክ በመዲናዋ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረጉ ይታወሳል። የትራንስፖርት መስተጓጎል እና እጥረት እንዳይከሰት አሊያንስን ጨምሮ ሌሎች አውቶብሶችን ለመተካት መታስቡን ከቢሮው ሰምተናል።

በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-07-01