ሀገሬ ቲቪ

ከሰል የአዕምሮ ጤንነት ይጎዳል ተባለ

በቤት ወስጥ ለማብሰያነት የምንጠቀማችው ተቀጣጣይ ነገሮች በሴቶች የአእምሮ ጤንነት ላይ ተጽዕኖ አሳድረዋል ተባለ።

በተለይ በአፍሪካ ፣ በእስያና በማዕከላዊና በደቡብ አሜሪካ የሚኖሩ 2.6 ቢሊዮን ገደማ ዜጎች ምግብ ለማብሰል ወይንም ለመብራት እንደ እንጨት፣ ከሰል አሊያም ጋዝን ይጠቀማሉ ይላል፤ በእንግሊዝ የተደረገ አንድ ጥናት።

በዚህም ምክንያት በየዓመቱ ከ2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ያለ ዕድሜያቸው ይሞታሉ፡፡ በተጨማሪም ለአዕምሮ ችግር፣ ለሳንባ ካንሰር፣ ሥር ለሰደደ የሳንባ በሽታና ለልብ ሕመም ለመሳሰሉት የመተንፈሻ አካላትና የደም ዝውውር በሽታዎች ያጋልጣሉ።

በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-07-01