ሀገሬ ቲቪ

አሽከርካሪዎችን ግራ የሚያጋባው መንገድ

ካሻን ተነስተን ወደ ሻትንበት ያሻግረናል። የሀገሬው ሰው ከቤቱ ውጥቶ ጉዞ ከመጀመሩ አስቀድሞ ወዳጅ ዘመድ ተሰብስቦ በሰላም ካሰበበት እንዲደርስ መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ፤ ሲል ይመርቀዋል።

ታዲያ ከቤተዎ ተመርቀው የጀመሩት መንገድ ግራ ቢያጋባዎትስ። ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ በሰላም ለመድረስ ስርዓት ባለው መንገድ ላይ በስርዓት ማሽከርከርን ይጠይቃል።

ከወደሜክሲኮ ያለ ተራራማ መንገድ ግን እንደው ግራ መሆኑን ሰማን፤ እርስዎ የሚያውቁት መንገድ በስርዓት የተሰደረ አሽከርካሪዎች ወደ አንደኛው አቅጣጫ ሲያቀኑ የቀኝ ወይም የግራ አቅጣጫቸውን ብቻ ይዘው የሚጓዙብት፣ ለሚመጣ በሚፈቀደው አቅጣጫ በጭራሽ ለሚሄደው መኪና የሚከለከል ነው።

የሜክሲኮ ተራራማ ቦታ የሚገኝው መንገድ ግን ከዚህ በተለየ መልኩ ለአሽከርካሪዎች ግራ የሚያጋብ እንደሆነ እየተነገረለት ይገኛል። የሜክሲኮ አኩልዚንጎ አካባቢ ያለው ይህ መንገድ በእጅጉ ጠመዝማዛ ኩርባዎች የሚበዙበት ከመሆኑ የተነሳ ለአሽከርካሪዎች ፈተና እየሆነ ነው። በዚህ ፈታኝ መንገድ ላይ አሽከርካዎች እንዲያሽከረክሩ የሚገደዱበት መንግድ ግርምትን የሚያጭር ነው።

የእኛን ሀገር ጨምሮ በሌሎች ቦታዎች እንደምናውቀው አይነት መኪኖች አንድ መስመር ብቻ ይዘው ማሽከርከር አይችሉም።

ወደ ኩርባዎቹ ሲጠጉ መስመራችውን እንዲቀይሩ ይገደዳሉ። ብቻ መኪናዎን በመንገዱ ላይ አንዴ ወዲህ አንዴ ደግሞ ወዲያ እያደረጉ ማሽከርከር የግድ ይለዎታል።

የሀገሬው የመንገድ አስተዳዳሪ ተቋም ይንን ማድረጌ መንገዱ ላይ የሚንቀሳቀሱ ከባድ መኪኖች በመንገዱ ጠምዝማዛነት ሳቢያ ለአደጋ እየተጋለጡ በመምጣታው ነው ባይ ነው።

አሁን የእየተጠቀምኩት ያለው ዘዴ ለእነዚህ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች የተመቸ ከመሆኑም በላይ በዚህ መንገድ ላይ ይደርስ የነበረን አደጋ በእጅጉ ቀንሶታል እያለም ይገኛል ተቋሙ።

ታዲያ በዚህ መንገድ ላይ ለማሽከርከር እድሉ ከገጠሞ አይኖዎን ከመንገዱ ሳይነቅሉ እያንዳንዷን የመንገድ ምልክት በትኩረት በማየት ማሽከርከር የግድ ይልዎታል።

በአንድ የመንገድ ምልክት እና በሞት መካከል ያለው ልዩነት የክር ያህል የቀጠነ ነው። ተሳፋሪም ሆነው በዚህ መንገድ መጓዝ ነብስ እና ስጋን ማላቀቅ ነው። እርሶ የተሳፈሩበት መኪና በሚሄድበት መስመር ከተቃራኑ አቅጣጫ የሚመጣ መኪናን መመልከት የተለመደ ነው፡፡ በተለይ በጭጋጋማ ጊዜያት መንገዱ በእጅጉ የሚያስፈራ ነው።

ይህ ጊዜ የአሽከርካሪዎቹን ጠንቃቃነት አብዝቶ ይፈልጋል። እንዲህ ያሉ መንገዶች አይደለም እንዲህ ያለው ውስብስብ የመንገድ ላይ ምልክቶች ተጨምረውበት በለመድነውም መንገድም አስፈሪ ናቸው።

መቼም አባይ በርሃን ያቋረጠ እና ሊማሊሞን የወጣ ስሜቱን ያውቀዋል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-07-04