ሰዎች ያሉባቸውን እንደ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ አልፍ ሲልም ፖለቲካዊ ችግሮች ለመፍታት በኅብረት መደራጅት መፍትሄ መሆኑን በመገንዝብ በ1887 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የኅብረት ሥራ ማህበራት ተቋቋመ ።
ይህ ማኅበር ታዲያ ከ1919 ዓ.ም. ጀምሮ በሐምሌ ወር የመጀመሪያ ቅዳሜን ተገን በማድርግ በዓለም ዙሪያ ይከብራል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ደግሞ ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ባህላዊ ዕድገት ውስጥ የኅብረት ሥራ ድርጅቶች ወሳኝ ሚና እንዳላቸው በማመን እውቅናቸውን ዳግም አረጋግጧል።
ዘንድሮ 100ኛውን ዓለም አቀፍ የኅብረት ሥራ ማህበራት ቀን “የኅብረት ሥራ ማህበራት የተሻለ ዓለም ይገንቡ” በሚልመፈክር ሰኔ 27 በዓለም ዙሪያ ተከብሯል።
የኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ወ/ሮ አያልሠው ዳንኤል በኢትዮጵያም “ኀብረት ሥራ ማኅበራት ለተሻለች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል 14ኛው የኅብረት ሥራ ማኅበራት ቀን ቀደም ብሎ ሰኔ መጀመሪያ ተከብሯል ይላሉ።
ማኅበራቱ በተለይ ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ የኅብረት ስራ ህግ በጠበቀ መልኩ አባላቶቻቸውን ብሎም ሌላውን ህብረተሰብ ማገለገል እንዲችሉ በወጣው አዋጅ መሰረት ተደራጅተው እየተነቅሳቅሱ ነው።
አሁን ላይ 24 ሚሊዮን የግለሰብ አባላትን ይዟል።
ከኅብረት ስራ ማኅበራቱ ውስጥ አብዛኞቹ እጅግ ውጤታማ ሲሆኑ ግብርና ከፍተኛውን ስፍራ ይይዛል ይላሉ ከሀገሬ ቲቪ ጋር ቆይታ ያደረጉት ወ/ሮ አያልሠው ዳንኤል ተናግረዋል ።
ማኅበራቱ በተደጋጋሚ የሚነሱባቸው ቅሬታዎች መካከል ዘመናዊ አሰራርን አለመከተል፣በተማረ የሰው ሃይል አለመመራት ለአባላትም ይሁን ለተገልጋይ ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዳይሰጡ አድርጎቸዋል።
የመስሪያ ቦታ እጥረት ከመንግሥት በኩል መሬት አሊያም ቢሮዎቸን የማግኝት መብት ቢኖራቸውም የመንግሥት አስፍጻሚዎቸ ይህንን ለማድረግ ፍቃድኛ አይደሉም በሚል ያስውቅሳቸዋል።
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመጥቀም ረግድ ጥራት ያለው ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረቡ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆነ በቅርቡ በተጀመረው የእሁድ ገበያ ላይም 57 ቦታዎች ላይ 219 ማህበራት እየተሳተፉ ነው።
ተቋማቱ ከፍተኛ ገንዘብ የሚንቅሳቀሰባቸው እንደመሆናቸው ከሙስና ጋር በተያያዘ ስማቸው እንደሚንሳ ያልሸሽጉን ኅላፊዋ የተደራጁ ዘመናዊ አስራሮቸን ለመስራት ዝግጅት ማደርጋቸውን እና እስካሁን ጥፋት የተገኝባቸው አካላት ላይ እርምጃዎች ተወስደዋል ይላሉ።
60 ዓመታትን ያስቆጠረው ዘርፉ የገንዘብ ፣ የግብርና እና መስል ተቋማትን ያካተተ ነው።
በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-07-04
