ጊዜው 1902 ነው። በአሜሪካ የዘረኝነት ጥላ እንደተንሰራፋ ነው።
የነጭ ቆዳ ቀለም ባለቤቶች የበላይነት በስፖርቱም ጭምር በሁሉም ዘርፍ ይቀነቀናል።
የቦክስ ስፖርት ደግሞ የነጭ የበላይነት ከሚቀነቀንባቸው የጊዜው የስፖርት እንቅስቃሴዎች አንዱ ነው።
በዚሁ በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በዛሬዋ ዕለት በቦክሱ መድረክ ጆንሰን የተባለ ጥቁር በአሸናፊነት ደመቀበት።
በሬኖ ኔቫዳ ፍልሚያውን ለመመልከት 22 ሺህ ተመልካቾች ታድመዋል።
በሀገረ አሜሪካ በተለያዩ አዳራሾች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ስለጨዋታው የሚተላለፉ የቴሌግራፍ ዘገባዎችን በቀጥታ ለመስማት ታድመዋል።
ጃክ ጆንሰን የተባለ ጥቁር ቦክሰኛ ጀፍሪ በተባለው ነጭ ተፋላሚው ላይ ገና ከመጀመሪያው በፍልሚያው የበላይነቱን ያሳይ ጀመር።
በአሸናፊነትም አጠናቀቀ።
የመጀመሪያው ጥቁር የቦክስ ስፖርት አሸናፊ ጃክ ጆንሰን። የጨዋታው ውጤት በመላ አሜሪካ ዘር ተኮር ግጭት እና ብጥብጥ አስነሳ።
የከባድ ሚዛን የቦክስ ስፖርት አሸናፊ መሆን የቻለው የመጀመሪያው አፍሪካ አሜሪካዊ ጃክ ጆንሰን ብዙ ነጭ ተፋላሚዎችን በቦክሱ ዓለም በማሸነፍ የጊዜው የነጭ የበላይነት ትርክትን ተገዳድሯል።
ይሄው በአሸናፊነት ከሚታወሱ የቦክስ ስፖርተኞች አንዱ የሆነው እና የጋልቭስቶን ግዙፉ ሰው ተብሎ የሚጠራው ጃክ ጆንሰን የተወለደው በቴክሳስ ጋልቭስቶን በ1870 ዓ.ም. ነበር።
የተወለደው ቀድሞ ባሪያ ከነበሩ ወላጆች ሲሆን ከዘጠኝ ልጆች ሶስተኛው ነው።ቤተሰቦቹን ለማገዝ ከአምስተኛ ክፍል ትምህርቱን ያቋረጠው ጆንሰን በጋልቫስቶን ወደቦች የጉልበት ስራ ጀምሯል።
ጠንካራ ተፋላሚ መሆኑን ቀደም ብሎ መገንዘብ ቢችልም ነጭ አሸናፊዎች ጥቁር ተፋላሚን ለመግጠም ያላቸው ፈቃደኝነት አነስተኛ መሆን የተፋላሚነት እድሎቹን ጠባብ አድርጎታል።
ያገኘውን እድል በመጠቀም እ.ኤ.አ. በ1903 ጆንሰን የአለም የከባድ ሚዛን የቦክስ ፍልሚያ አሸናፊ ሆነ።
በአመቱ ከጂም ጀፍሪ ጋር የፍልሚያ እድል አገኘ።
ጂም ጀፍሪ በወቅቱ ስመ ገናና የሆነ ነጭ አሜሪካዊ ቦክሰኛ ነው። ጀፍሪስ ጆህንሰንን ለመግጠም ፈቃደኛ አልነበረም።
ኋላም ጆንሰን የካናዳው ነጭ ቦክሰኛ ቶሚ በርንስን አሸንፏል።
በ1900 ዓ.ም ከካናዳዊው በርንስ በአውስትራሊያ ሲድኒይ በባህር ዳርቻ የገጠመው ጆንሰን በ20 ሺህ ታዳሚዎች ፊት በማሸነፍ የአለም ከባድ ሚዛን አሸናፊ ለመሆን ችሏል። ወደ አሜሪካ ሲመለስ ግን የተደረገለት አቀባበል እምብዛም ነበር።
ነጭን በማግባቱ እና ባለው አኗኗር ዘረኞችን አስደንግጧል። ለትችታቸው ግን እጅ አልሰጠም።
ዘጋቢዎች ታላቁ የነጭ ተስፋ የአለም ሻምፕዮን ወይም አሸናፊ የሚለውን ማዕረግ ያስመልሳል ሲሉ መጣራት ጀመሩ። ጆንሰንን የሚበግር የአሜሪካ ተፋላሚ ጠፋ። ብዙዎችን አሸነፈ።
ኋላም የአለም አሸናፊ ጂም ጀፍሪ ሊፋለመው ፈቃደኛ ሆነ።
የሁለቱ ፍልሚያ የክፍለ ዘመኑ ፍልሚያ ተብሎም ይጠራል። በሬኖ ኔቫዳ ፍልሚያው ዝግጁ ሆነ።
በዛሬዋ ዕለት ከክፍለ ዘመን በፊት በ1902 ዓ.ም. ስመ ገናና የቦክስ ነጭ ተፋላሚ የነበረውን ጂም ጀፍሪን በማሸነፍ ጆንሰን የመጀመሪያው ሆነ።
የአለም ሻምፕዮን ወይም አሸናፊ የሚለውን መጠሪያ በእጁ አስገባ። በቦክሱ ስፖርት ጫፍ አናት ላይ ጥቁርን መመልከት የማይሹ የነጭ ደጋፊዎች ቁጣ ተቀሰቀሰ።
ውጤቱን ተከትሎ በአሜሪካ ዘር ተኮር ብጥብጥ እና ግጭት ተቀሰቀሰ።
የጆንሰንን ድል ለማክበር የተሰባሰቡ ጥቁሮች ጥቃት ተፈጸመባቸው።
የተቆጡ ነጭ ደጋፊዎች ጥቁሮች ላይ ጥቃት አደርሱ።
ለአሸናፊነቱ ጆንሰን 117 ሺህ ዶላር ማግኘት ችሏል።
ለአምስት አመታትም የአለም አሸናፊ ወይም ሻምፕዮን የሚለውን መጠሪያ በእጁ አድርጓል።
ጃክ ጆንሰን በ1938 ቢያርፍም የመጀምሪያው ጥቁር የአለም ሻምፕዮና 73 ፍልሚያዎችን በማሸነፍ ያጠናቀቀ በቦክሱ ስፖርት የነጮችን የበላይነት የሰበረ ሰው ተደርጎ ይታወሳል።
በአብርሃም በለጠ
2022-07-04
