የግብርና ሚኒስተር ከብራዚል የግብርና ሚኒስተር እና ባለሙያዎች ልኡካን ጋር የልምድ ልውውጥ እና የመስክ ጉብኝት ማድረጉ ተገለጸ።
የብራዚል ልኡካን በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሲዳማ ክልሎች ለአምስት ቀናት የመስክ ጉብኝት አድርገዋል።
ልኡካኑ በሶስቱ ክልሎች ያሉ የተለያዩ የግብርና ምርቶችን የአዝርእት፣ የአትክልት እና የፍራፍሬ ብሎም የእንስሳት እርባታን እና የመስኖ ስፍራዎችን ጎብኝተዋል።
የግብርናና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር መለሰ መኮንን ጉብኝቱ ከብራዚል ልኡካን እና ባለሙያዎቹ ጋር በመተባበር የአርሶ አደሮችን ህይወት ለማሻሻል እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።
በአብርሃም በለጠ
2022-07-04
