ሀገሬ ቲቪ

ትርፋማው ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ ተቋም

ኢ-ቴክ አክሲዮን ማህበር በተቋቋምኩበት ዓመት አትርፌያለሁ አለ፡፡ በመላው ዓለም በሚኖሩ 525 ባላክሲዮኖች በ200 ሚሊዮን ብር ካፒታል ስራውን የጀመረው አክሲዮን ማህበሩ በተመሰረተበት ዓመት ወደ ስራ በመግባት ትርፋማ መሆን እንደቻለ ተጠቁሟል፡፡ አክሲዮን ማህበሩ የባለአክሲዮኖች ሦስተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ባደረገበት ወቅት ነው ይህንን ያለው፡፡ በአይ.ሲ.ቲ ዘርፍ ሀገር በቀል አክሲዮን ማህበር የሆነው ተቋሙ በሀገሪቱ ተፈላጊ የሆነውን የ አይ.ሲ.ቲ ዘርፍ ጉድለትን ለመሙላት ስለመቋቋሙ ተነስቷል፡፡ አክሲዮን ማህበሩ በሀገራችን በውጭ ኩባንያዎች የሚከወኑትን የአይ.ሲ.ቲ. መሰረተ ልማት ዝርጋታዎችን በሀገር በቀል ተቋም ለመተካት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በያዝነው ዓመትም በዓለም አቀፍ ደረጃ በዘርፉ የሚከናወኑ መሰረተ ልማቶች ላይ ለመሳተፍ ይረዳኝ ዘንድ በአሜሪካ እና በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ዱባይ ላይ ቢሮዎችን ለመክፈት ቅድመ ዝግጅት አድርጌአያው ብሏል፡፡ ይህንንም ለማሳካት በጥር መጀመሪያ የሚተገበር ዕቅድ ማዘጋጀቱን ገልጿል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-13