ሀገሬ ቲቪ

በሊቢያ ያለው ቀውስ እንዲቆም ተጠየቀ

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በሊቢያ ያለውን ሁኔታ አስመልክተው መግለጫ አውጥተዋል። ሊቀመንበሩ አሥር ዓመታትን የተሻገረው በሀገሪቱ ያለው ቀውስ በፍጥነት እንዲያበቃም ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።

በሊቢያ ያለው ህዝባዊ ንቅናቄም የሁሉንም ዜጎች፣ የግለሰብ እና መንግሥት ተቋማትን ጥፋት የማያደርስሊ ሆን እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በሀገሪቱ ያለው ህዝባዊ ንቅናቄ በሀገሪቱ ያሉ ሁሉንም አካላት እና የህዝብን መብቶች ያከበሩ መሆን አለባቸውም ብለዋል።

ሊቀመንበሩ አያይዘም በሊቢያ ይደረጋል የተባለው ብሔራዊ እርቅና መግባባት ሁሉን አቀፍ እና የሊቢያ ህዝብን ባለቤት ያደረገ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-07-04