ሀገሬ ቲቪ

የእንግሊዝ ጦር ዩቲዩብ እና ትዊተር አካውንቶች ተጠለፉ

የእንግሊዝ ጦር የዩቲዩብ ቻናሉ እና ትዊተር ገጹ መጠለፋቸውን አስታወቀ።

በዩቲዩብ ቻናሉ የቢሊየነሩ ኤለን መስክ ክሪፕቶ ከረንሲ የመጠቀም ምስሎች ተለጥፈውበታል። በትዊተር ገጹም ብዙ ለኢንቨስትመንት የሚያገለግሉ የኤሌክትሮኒክ ጥበብ ሥራዎች እንደተላለፉበት ተጠቁሟል።

ጦሩ ጉዳዩን በቁም ነገር እንደተመለከተው እና የመረጃ ደህንነት ጥሰት እንደተፈጸመ ብሎም ችግሩ እንደተፈታ አስታውቋል።

የጦሩን የዩቲዩብ ቻናሉንም የትዊተር ገጹንም ማስመለስ ተችሏል።

በአብርሃም በለጠ
2022-07-04