ሀገሬ ቲቪ

የሞቾች ቁጥር 800 ሺሕ የደረሰባት አሜሪካ

በአሜሪካ በኮሮና የሟቾች ቁጥር ከ800 ሺሕ በልጧል ይህ የሟቾች ቁጥር በ2ተኛው የዓለም ጦርነት ከሞቱት በእጥፍ የበለጠ ሆኗል፡፡ በቫይረሱ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከዋሽንግተን ዲሲ አሊያም ከቦስተን ከተማ ነዋሪዎች ይልቃል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ በንጽጽር ሲቀመጥ የሟቾች ቁጥር ከ2020 ዓመት ይልቅ እየተገባደደ በሚገኘው 2021 ከፍተኛ ሞት ተመዝግቧል፡፡ እስካሁንም በአሜሪካ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 50 ሚሊዮን ተጠግቷል፡፡ ከፍተኛው የሞት መጠን በአሜሪካ የተመዘገበው ባልተከተቡ ሰዎች እና እድሜያቸው በገፉ አዛውንቶች ላይ መሆኑን ሪፖርቶች አመላክተዋል፡፡ ባለፉት 11 ሳምንታት ብቻ 100ሺሕ ሰዎች በአሜሪካ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ቫይረሱ በከፍተኛ ፍጥነት ለሰዎች ህልፈት ምክንያት እየሆነ መምጣቱም ተጠቁሟል፡፡ ብራዚል በወረርሽኙ 616ሺሕ ሞት ሲመዘገብባት በሟቾች ብዛት በሦስተኛ ደረጃ በምትቀመጠው ህንድ ደግሞ ከ475ሺሕ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-15