ሀገሬ ቲቪ

የሆቴል መገልገያ መሳሪያዎች የንግድ ትርኢት ሊዘጋጅ ነው

ግራንድ ኤልያና ሆቴል የሆቴል ግበዐት አቅራቢዎችን ከተለያዩ ባለ ድራሻ አካላት ጋር የሚያገናኝ ኤክስፖ ከ ሀምሌ 12 እስከ 13 ሊያዘጋጅ መሆኑን አስታውቋል። ይህ ኤክስፖ በሀገር ውስጥ ያሉ የተለያዩ የሆቴል ግብአት አቅራቢዎች ከሆቴሎች ጋር የሚገናኙበትን እድል ለመፍጠር ታስቦ የሚዘጋጅ ሲሆን በዋናነት አላግባብ የሚወጡ የውጪ ምንዛሬዎችን ለመቅረፍ አላማ አለው ተብሏል ።

ኤክስፖው የውጪ ምንዛሬን ማስቀረት አቅራቢዎችና ገዢዎች ፍላጎታቸውን በቀላሉ ለማሟላት እንዲሁም ከሆቴል ኢንዱሰትሪው ጋር በቀጥታ የተያያዘ ምርታቸውን ለማስተዋወቅ ከማገዙ ባለፈም ከኮቪድ በኋላ የተዳከመውን የሆቴል ኢንዱስትሪ ለማነቃቃት ጉልህ ድርሻ እንዳለው አዘጋጆቹ ተናግረዋል ።

በዚህ ኤክስፖከ 200 ተሳታፊዎች እና ከ10 ሺህ በላይ ጎብኚዎች ይገኛሉ የተባለ ሲሆን በሆቴል ስራ ለመሰማራት የሚፈልጉ አዳዲስ ባለሀብቶች የበለጠ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።

የሆቴል ማሰልጠኛ ተቋማት ፣ባንኮች ፣ ፣ አየር መንገድ ፣ የምግብ እና መጠጥ እንዲሁም የንፅህና መጠበቂያ አቅራቢዎች የሚሳተፉ ሲሆን ማንኛውም ሰው በመምጣት የዝግጅቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-07-06