የነዳጅ ድጎማ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ገለጸ። በመላ ሀገራችን ለሚገኙ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርገው የነዳጅ ድጎማ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን መጀመሩ ተነግሯል።
በኢትዮ ቴሊኮም በኩል በበለጸገው መተግበሪያ የተመዘገቡ ከ160 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች በቴሌ ብር መተግበሪያውን በመጠቀም አገልግሎቱን ከዛሬ ጀምሮ ማግኘት መጀመራቸው ነው የተገለጸው። የተሽከርካሪዎቹ ዓመታዊ የነዳጅ ፍጆታ ግምት በጥናት መለየቱም ተጠቁሟል።
በአብርሃም በለጠ
2022-07-06
