
ኬኒያ በአፍሪካ ቁጥር አንድ የአቮካዶ ላኪ ሀገር ሆነች። በአቮካዶ ምርት ቁጥር አንድ የነበረችውን ደቡብ አፍሪካን በመቅደም ነው የደረጃውን አናት የተቆናጠጠችው።
በሀገሪቱ ማዕከላዊ ግዛት የሚገኙ ገበሬዎች የቡና ተክሎችን በአቮካዶ እየተኩ ይገኛሉ። በሀገሪቱ ያሉ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ፋብሪካዎችም ወደ ውጪ የሚላኩ አቮካዶዎችን ጥራት መፈተሽ ብቻም ሳይሆን ቅርፅ እና መጠናቸውንም እንደሚለኩ ተዘግቧል።
ይህም በዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ የኬኒያ አቮካዶዎች ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ማድረጉን ካፒታል የተባለ ድረ ገጽ አስነብቧል።
በሳምሶን ገድሉ
2022-07-06