6ኛዉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) በተገኙበት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል።
ከምክርቤቱ አባላትም ለጠ/ሚኒስትሩ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄ ቀርቦላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።
የጸጥታ ችግር፣ የሽብር ቡድንን ጥቃት፣ ሀገር አቀፍ ፈተና ፣ዘር ተኮር ጥቃቶችን፣ የዜጎች ግድያ እና በርካታ ጉዳዮችን ከጥያቄዎቹ መካከል፤ የጸጥታ ችግር ከመፈጠሩ በፊት አስቀድሞ መከላከል አይገባም ነበር ወይ? የንጹሀንስ ሞት መቼ ያቆማል? በቀጣይስ እንዳይከሰት መንግሥት ምንድነዉ እቅዱ? እና ሊሎቸም ተነስተዋል በትህነግ እና በኦነግ ሸኔ በአማራ፣በመሃል ሀገር በሎም በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚፈጸም ጥቃት ቢኖርም መንግሥት ተደምሦል የሚል ምላሽ ቢሰጥም ዛሬም ንጹሃን እያልቁ ነው ተብሏል።
በቀጣይ ዓመት በኦንላይን ይሰጣል ለተባለዉ ሀገር አቀፍ ፈተና ይገባሉ የተባሉ 1 ሚሊዮን ታብሌት ኮምፒውተሮች ሂደት ተስተጓጉሏል ፤ ለ2015 ፈተና መንግሥት ምን እያከናወነ ነዉ እንዲሁም ከትግራይ ክልል ህዝቡ ለሚያሰማዉ ሰቆቃ ፣
በኢትዮጲያ የተፈፀሙ ዘር ተኮር ጥቃቶችን ለማውገዝ የሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች መከላከል እንደሌለባቸው ተጠቁሟል። እስከ አሁን በተደረጉት የተቃውሞ ሰልፎች 12 ሰዎች ተገለዋል ከ100 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል ሲሉ አባሉ አንስተዋል።
ጠ/ሚኒስትር አብይ በመልሳቸዉ የሽብር ቡድኖች የሚፈጽሟቸዉ ጥቃቶች የሚፈጠሩ የጸጥታ ስጋቶችን ለማረጋጋትም የጸጥታ አካላት ዉድ ህይወታቸዉን እያጡበትም ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።
ለአብነትም በቅርቡ በወለጋ ደምቢዶሎ እና ጊምቢ ፣ ጋምቤላ ፣ አሙሮ በተከታታይ በተፈጸመሙ ጥቃትቶች በርካታ የጸጥታ ሀይሎች ህወታቸዉን አጥተዉበታል ብለዋል። ደራሼ ላይም የወረዳ አመራሮችን እና የጸጥታ አካላትን ጨምሮ 80 የሚሆኑ ሰዎች ህይወት አልፏልም ማለታቸዉን ከዚህ በተጨማሪም ጠ/ሚ አብይ ከሚፈጸሙ ጥቃቶች የበርካታ ንጹሀንንም ህይወት መታደግ ችለናልም ብለዋል።
የመካለከያ እና የደህንነት ተቋማት ባለፉት 15 እና 20 ዓመታት ከነበሩበት በእጅጉ የተሻለ ቁመና ላይ መሆናቸውን እና ይህን ያደረግነው የሽብር ኃይሎች ኢትዮጵያን ለማፈረስ ያላቸውን መሻት ስለምናውቅ ነው ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ካነሷቸው ነጥቦች ውስጥ በ2015 በጀት ረቂቅ ላይ ለምክር ቤቱ አባላት በሰጡት ማብራሪያ በጀቱ በስድስት ጉዳዮች ላይ ማተኮሩን አብራርተዋል፡፡
የበጀት ዓመቱ የትኩረት አቅጣጫዎችም÷ ብድር መቀነስ፣ የበጀት ጉድለት መቀነስ፣ ያለንን ሀብት በቁጠባ መጠቀም፣ የዋጋ ንረትን ማረጋጋት ፣መልሶ ማቋቋምና ሰብአዊ እርዳታ እንዲሁም የሀገር ደህንነት እና ሰላምን ማስጠበቅ ናቸው፡፡
መንግስት ገቢ እስከ ግንቦት ድረስ 300 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 309 ቢሊዮን ብር ተሰብስብቧል፤ አምና በ11 ወር የተሰበሰበው የዘንድሮው 50 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስተሩ።
በ11 ወራት ውስጥ 500 ቢሊዮን ብር ወጪ የወጣ ሲሆን ወጪው ያበዛው ለእዳ ተከፍሏል፤ከገቢያችን ውስጥ 1 ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ዶላር እዳ ተከፍሏል። ዘንድሮ በቡና ገበያ ከአፍሪካ ትልቁን መጠን ኤክስፖርት አድርገናል ብለዋል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት በሰራነው ስራ ግን በሁለት ዓመት ውስጥ ከአንድ ቢሊየን በላይ በመጨመር በሸቀጦች የወጪ ምርት ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል። በአገልግሎት ደግሞ በ25 በመቶ አድጎ ስድስት ቢሊየን ዶላር በላይ አግኝተናል፤ ኢትዮጵያ ከውጪ ንግድ 10 ቢሊየን ዶላር ገቢ አግኝታልች ሲሉ ለምክር ቤቱ አብራርተዋል።
በጦርነት የወደሙ አካባቢዎች ላይ የተመደበው በጀት በሚመለከት ከምክር ቤቱ አባላት ጥያቄዎች ተንሰተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወልቃይት ሲታስብ በተመሳሳይ የትግራይን ታሳቢ ማደርግ ያሰፈልጋል ለክለሉ መንግሥት ኅላፊንቱን ሰተናል ይላሉ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ውሎው 786 ነጥብ 61 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን የ2015 የፌዴራል መንግስት በጀት በአራት ድምጸ ታአቅቦ አጸድቋል፡፡
ከ2014 በጀት ዓመት በጀት ጋር ሲነጻጸር የ111 ነጥብ 94 ቢሊየን ብር ወይም የ16 ነጥብ 59 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-07-07
