ሀገሬ ቲቪ

የቦስተን ድጋፍ ለኢትዮጵያ

89 ሺሕ ዶላር የሚያወጡ 17 ቬንትሌተሮች ለጤና ሚኒስቴር ድጋፍ ተደረጉ፡፡ የቦስተን ታክስ ፎርስ ከቦስተን የኢትዮጵያውያን ስፖርት ክለብ ጋር በመተባበር ነው ድጋፍ ያደረጉት፡፡ ክለቡ በኢትዮጵያ ለአሜሪካ ኢምባሲ ያስረከቧቸው ቬንትሌተሮች ለጤና ሚኒስቴር መላካቸውን ተሰምቷል አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳሰፈሩት ክለቡን እና ማሽኖቹን በመመርመር ጭምር ሙያዊ ድጋፍ የሰጡትን አቶ እሸቴ ወልደየስን አመስግነዋል፡፡ አምባሳደር ጨምረው እንዳስታወቁት ቬንትሌተሮቹ እስኪጫኑ የመጋዘንና ተያያዥ ወጪዎችን ለሸፈነው ለናታን ትራቬል እና ካርጎ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በማመስገን ሌሎችም ተመሳሳይ ድጋፍ እንደሚያደርጉ እምነታችን ነው ብለዋል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-15