በዓለማችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተከሰተው የዝንጀሮ ፈንጣጣ የስርጭት ኹኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የዓለም ጤና ድርጀት መረጃ ያሳያል። አኹን ላይ በሽታው 6 ሺህ ሰዎችን ስለማጥቃቱ ድርጅቱ አስታውቋል። ከኹለት ወራት በፊት ስለዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ መከሰት በይፋ ከተነገረ በኋላ እስካኹን ድረስ 58 ሀገራት ላይ ተከስቷል።
ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ጀርመን፣ ካናዳ እና ሊሎች የአውሮፓ ሀገራትን እንደ አብነት ማንሳት ይቻላል።
የዓለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣን እንደኮቪድ 19 ቫይረስ ዓለም አቀፍ ወረርሺኝ ሲል ብያኔ እንዳልሰጠው ነው በጉዳዩ ላይ የወጡ መረጃዎች የሚያሳዩት። ከዚኽ ቀድም በጉዳዩ ላይ በተደረገ ውይይት በሽታው ዓለም አቀፍ ስጋት እንዳልኾነ ተገልጾ እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል። ድርጅቱ በሽታው ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ አሊያም ሥጋት አይደለም ይበል እንጂ በአውሮፓ ሀገራት የዝንጀሮ ፈንጣጣ በስፋት መሰራጨቱን ቀጥሏል።
የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራትም ቫይረሱን አግኝተናል ሲሉ በይፋ ሪፖርት አድርገዋል። ከዚህ ቀደም የዝንጀሮ ፈንጣጣ ያልተከሰተባቸው የአፍሪካ ሀገራት አኹን ላይ ሪፖርት እያደረጉ ስለኾናቸው የዓለም ጤና ድርጅት ዶ/ር ቴውድሮስ ተናገረዋል።
አኹን ላይ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴውድሮስ አድሀኖም የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ወቅታዊ መረጃዎች እና የስርጭት አድማሱ በድጋሜ ሊጤን እንደሚገባው ተነግረዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም ከበሽታው ምርምርራ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ተግዳሮቶች መኖራቸውም ገልጸዋል።
የበሽታው የስርጭት አድማስ እየሰፋ ቢሔድም የዓለም ጤና ድርጅት ግን እጄን አጣጥፌ አልተቀመጥኩም ከተለያዩ ሀገራት እና ክትባት አምራቾች ጋር በጋር ስለክተባቱ እና በእኩል ማዳረስ ስለሚቻልበት ብልሀት እየመከርኩ ነው ብሏል።
በተጨማሪም ከበሽታው ጋር በተያየዘ በሰዎች ላይ የሚደርሰውን መገለል የመስበር እና ዜጎች የዚህ ድርጊት ተጠቂ እንዳይኾኑ የመከላከል ተግባር እያከናወንኩ ነው ብሏል የዓለም ጤና ድርጅት።
በበሽታው ተይዘው ሪፖርት ከሚደረጉ የማኀበረሰ ክፍሎች ውስጥ ግብረሰዶማውያን ሰፊውን ቁጥር እንደሚወስዱ ነው ሲኤን ኤን የተሰኘው የዜና ምንጭ የዘገበው። ከዚህ ባለፈ ግን በዝንጀሮ ፈንጣጣ ከተጠቃ ሰው ጋር አካላዊ ንክኪ በማድረግ፣ ሕመምተኛው የተጠቀማቸውን ቁሶች ሳያጸዱ በመጠቀም፣ ከሕመምተኛው ጋር አልባሳትን መጋራት በሽታው የሚተላለፍባቸው መንገዶች ናቸው።
ይህ ጉዳይ የአህጉራችንም ራስ ምታት መኾኑ አልቀረም 11 የአፍሪካ ሀገራት በይፋ በዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የተያዙ ዜጎችን ማግኘታቸውን አሳውቀዋል። ለአብነትም ጎረቤት ሀገር ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ ኮንጎ ናይጄሪያ፣ ላይቤሪያ፣ ኮቲዲቫር ካሜሮን ተጠቃሽናቸው።
በአህጉሪቱ ወደ 2000 የሚጠጉ ዜጎች በዚኹ በሽታ መያዘቸው ተረጋግጧል ከ70 በላይ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ትኩሳትና ጠንከር ያለ ራስምታት ፣ በቆዳ ላይ ውሀ የቋጠረ እብጠት እና ብጉር የሚመስል ሽፍታ መታየት፣ የጡንቻ ሕመምና የጀርባ ሕመም ከፍተኛ የድካም የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ምልክት ናቸው። እነዚኽን ምልክቶች ያስተዋለ ሰው በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋማት ሊሔድ እና ሊመረመር እንደሚገባ የጤና ባለሙያዎች አጽናኦት ሰጥተው ተነግረዋል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-07-07
