ዩክሬን በሩሲያ ተፈጽመዋል ያለቻቸውን ከ21ሺሕ በላይ የጦር ወንጀሎች እየመረመርኩ ነው አለች።
የዩክሬን አቃቤ ሕግ ከየካቲት ወር ጀምሮ በቀን ከ200 እስከ 300 የሚጠጉ ወንጀሎች ተፈጽመዋል ብሏል። የጦር ወንጀል ፈጽማለች የተባለችው ሩሲያ ክሱን ውድቅ አድርጋዋለች።
አቃቤ ሕጉ "ሲቪሎችን የገደሉ የሩሲያ ወታደሮች ሁሉም ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፤ ይህ የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው" ማለታቸውን ቢዝነስ ስታንዳርድ ጽፏል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-07-07
