ሀገሬ ቲቪ

አንድ ሚሊዮን ሰዎች የሀጅ ጉዞ ያደርጋሉ

በኮቪድ የእንቅሰቃሴ እገዳ ከተነሳ በኋላ በሳውዲ አረቢያ ዓመታዊ የሃጅ ጉዞ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል። በ2019 በዓለም ዙሪያ የሚገኙ 2.5 ሚሊዮን ሙስሊሞች በዓመታዊው በዓል ላይ ተካፍለዋል።

በ2020 ወረርሽኙ መከሰቱን ተከትሎ 10 ሺሕ ሰዎች ብቻ እንዲታደሙ መፈቀዱ ይታወሳል፤ባለፈዉ ዓመት ደግሞ 60 ሺሕ ምዕመናን ብቻ የሀጅ ስነስርዓት ላይ ታድመዋል።

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ጭንብል ማድረግን የሚያስገድደዉን ህግ ጨምሮ በርካታ የኮቪድ ገደቦችን ባለፈው ወር ማንሳቱ አይዘነጋም፡፡

በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-07-07