ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ከነሀሴ ጀምሮ የቴሌኮም አገልግሎት ልሰጥ ነው አለ። የመጀመሪያ አገልግሎቱን በድሬዳዋ ከተማ ይጀምራል ተብሏል።
እስከ ሚያዝያ 2015 ዓ.ም ድረስ ለ25 ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት አቅዷል።
ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የተጀመረው የቴሌኮም መሰረተ ልማት ኪራይ ዋጋ ላይ ከስምምነት አለመድረስን ጨምሮ ሌሎች ምክንያቶች ተቋሙ ባሰበው ጊዜ አገልግሎት ለመጀመር እንቅፋት እንደሆነበት ተናግሯል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-07-07
