የውጭ ማስታወቂያ በተለምዶ አጠራሩ የቢልቦርድ ሥራ ወጥነት ባለው መንገድ ባለመተግበሩ ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ችግሮች ይታያሉ።
የውጭ ማስታወቂያ ፈቃድ ሥርዓትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ኃላፊነት የተሰጠው የአዲስ አበባ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አዲስ አበባን ቴክኖሎጂ ቀመስ ከተማ ያደርጋታል ያለውን የህትመት ማስታወቂያን ወደ ስክሪን የመቀየሩን ስራ ጀምሯል።
ባለስልጣኑ ከፈቀደኩት ስታንዳርድ ውጭ ማስታወቂያቸውን ሰቅለዋል ያላቸውን ከ20 በላይ የማስታወቂያ ባለሙያዎች ላይ እርምጃ ወስዷል። ይህ አካሄድ ግን ከወዲሁ በማስታወቂያ ባለሙያዎች ቅሬታን እያስተናገደ ይገኛል ።
የኢትዮጵያ የውጭ ማስታወቂያ ማኅበር ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኢሳያስ ጋሻው የማስታወቂያ ቦርዶች መንግሥት ሲጠቀምባቸው ህጋዊ እኛ ስንጠቀምባቸው ደግሞ ህገወጥ እየሆነ ነው ብለውናል።
የየካ ክፍለ ከተማ ከ20 የሚልቁ የማኅበሩ አባላቶቻችን የማስታወቂያ ሰሌዳ አፍርሶብናል ብለውናል አቶ ኢሳያስ
ከህትመት ማስታወቂያ ወደ ስክሪን ማስታወቂያ የመሸጋገርን ጉዳይ ባለሥልጣኑ ሁለቴ ሊያስብበት ይገባልም ብለዋል፡፡
የማኀብሩ አባል አቶ አኪያ ተሾመና የማኅበሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ቦርሶማም በአቶ ኢሳያስ ሀሳብ ይስማማሉ
የየካ ክ/ከተማ የግንባታና ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ሱራፌል እሽቱ ወደ እርምጃ ከመግባቱ በፊት ማስጠንቀቂያ ለባለሙያዎቹ ሰጥተናል ሲሉ ለሀገሬ ቴሊቭዥን ተናግረዋል።
በማስታወቂያ ባለሙያዎቹ የሚነሳውን ወቀሳ የማይቀበሉት አቶ ሱራፌል ተቋሙ ህጋዊ አመራር የለውም እየተባለ የሚወራው ውሸት ነው ብለዋል።
ከፈረሱ የማስታወቂያ ቢልቦርዶች ጋር በተያያዘ በማስታወቂያ ባለሙያዎቹ የተነሳዉን ጥያቄ አቅርበን አቶ ሱራፌል ተከታዩን ምላሽ ሰተውናል።
የአዲስ አበባ ግንባታና ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ም/ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ደስታ ለመንግሥት የተሰሩ ማስታወቂያዎች የታለመለትን ግብ እንደመታ ተነሺ እንደሚሆን ከመሥራታቸው አስቀድመን ተናግረናል ብለዋል።
አቶ ገዛኸኝ ደስታ በ ከተማዋ የስክሪን ማስታወቂያዎች ዙሪያም የሚነሱትን ጥያቄዎች በተመለከተ ይህንን ብለውናል
ይኸው የማስታወቂያ ዘርፍ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሚንቀሳቀስበት ዘርፍ ነው።
በመቅደስ እንዳለ
2022-07-12
