ሀገሬ ቲቪ

ጀምስ ዌብ ሳተላይት ጥራት ያለው ምስል አነሳች

በታህሳስ 2014 ዓ.ም ወደጠፈር ያቀናችው ጀምስ ዌብ የተሰኘችው የጠፈር ቴሌስኮፕ። ከምድር በ1.5 ሚሊየን ኪሎሜትር ርቀት ላይ በመሆን ጥልቁን አፅናፈ ዓለም ፎቶ በማንሳት ጥራት ያለውን ምስል ልካለች።

ቴሌስኮፗ በአፅናፈ ዓለም የሚገኙ በርካታ ጋላክሲዎችን ለመመልከት እድልን ሰትታለች።

የመጀመሪያው ፎቶ ወደምድር የደረሰበትን ኩነት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ታድመውታል። የቴሌስኮፗ ተግባር በጠርፈር ምርምር ላይ የተሻለ እይታ እንዲኖር ታስችላለች ተብሎላታል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-07-12