
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የምስራቅ አፍሪካ ማኀበረሰብ መሉ አባል ኾኛለው አለች።የኮንጎ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክሪስቶፍ ሉቱንዱላ የሚመሩት የልኡካን ቡድን በታንዛኒያ በመገኘት ሀገራቸው የምስራቅ አፍሪካ ማኀበረሰብ አባል መኾን የሚያስችላትን ጉዳዮች አቅርበዋል።
አኹን ላይ ኮንጎ ሰባተኛዋ የማኀበረሰቡ አባል ሀገር ኾናለች። በአባል ሀገራቱ ነዋሪ የኾኑ ዜጎች ያለቪዛ ከአንዱ ሀገር ወደሌላው መጓዝ ይችላሉ።
በተጨማሪም ሀገሪቱ የምስራቅ አፍሪካ ማኀበረሰብ አባል መኾኗ ከዳሬሰላም እና ሞንባሳ ወደብ ከቀረጥ ነጻ ሸቀጦችን የማስገባት እና የማስወጣት ጥቅም ታገኛለች። ኬኒያ፣ ሩዋናዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ቡርንዲ፣ ታንዛኒያና ቡርንዲ የዚሁ ማኀበረሰብ አባል ናቸው።
በሙሉጌታ በላይ
2022-07-12