በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ እና በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ አዋሳኝ አከባቢዎች መካከል በተከሰተው ግጭት በፀጥታ አካላት እና በንፁኃን አርሶአደሮች ላይ የሕይወት መጥፋት እንዲኹም የአካል ጉዳት መድረሱን የወረዳው ኮምዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡
ግጭቱን የፈጠሩት የሸኔን አመለካከት ተሸክመው በሕዝቡ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተላላኪዎች ናቸው ተብሏል። በመኾኑም በወረዳው እና በከተማው ውስጥ የሚገኙ የሶስት እግር ተሽከርካሪዎችን (ባጃጆችን) ላልተወሰነ ጊዜያት በቀንም ሆነ በማታ ማሽከርከር እንደማይችሉ ተነግሯል።
ከፀጥታ ኀይልሎች ውጪ የጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ማንኛውም ግለሰብ ከቀበሌ ወደ ቀበሌ መንቀሳቀስ አይችልም ተብሏል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-07-12
