የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ። አቶ ምትኩ ካሳ በሙስና ወንጀል በመጠርጠራቸው ነው በዛሬው ዕለት በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት።
"ኤልሻዳይ" ከተሰኘ በጎ አድራጎት ማኀበር ባለቤት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል እንደተጠረጠሩ በፌዴራል ፖሊስ በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው ተናግረዋል።
ግብረሰናይ ድርጅቱ በአዋሽ፣ በአዳማ፣ በሀዋሳ፣ በእንጅባራ እና በሌሎችም አካባቢዎች ተፈናቃዮች በሌሉበት በተደጋጋሚ ጊዜ የእርዳታ እህልና አልባሳት በመረከብ ሽጦ ለተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት መግዛቱ በምርምራ መረጋገጡ ተነግሯል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-07-13
