ሀገሬ ቲቪ

የሰላም አማራጭ ዐብይ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባ

በምክትል ጠ/ሚ እና የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራው እና በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተቋቋመው ዐብይ ኮሚቴ በይፋ ሥራ መጀመሩን አስታቋል።

ኮሚቴው የፌደራል መንግሥቱ ከህውሓት ጋር የነበረውን ጦርነት በድርድር ለመፍታት የተቋቋመ ነው።

ኮሚቴው የመጀመሪያውን ስብሰባ ማካሔዱንም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔ ራዊ ደህንነት አማካሪ እና የዐብይ ኮሚቴው አባል አቶ ሬድዋንሁሴን በቲውተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-07-13