ሀገሬ ቲቪ

የሴሪላንካ ጠቅላይ ሚኒስትር ኮበለሉ

የሴሪላንካ ጠቅላይ ሚኒስትር ጎታባያ ራጃፓክሳ ሀገሪቱን ጥለው ኮብልለዋል ተባለ።

የሀገሪቱ ምጣኔሀብት በእጅጉ ቀውስ ውስጥ መግባቱን ተከትሎ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ፕሬዝዳንቱ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥልጣን ይነሱ የሚል ሰፊ የሕዝብ ተቃውሞ እየተካሔደ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ራጃፓክሳ ከሥልጣን መነሳታቸውን ይፋ ያደርጋሉ ሲባል እሳቸው ግን ሀገሪቱን ጥለው የሲሪላንካ ጎረቤት ወደ ኾነችው ማልዲቭስ መኮብለላቸውን የሀገሪቱ የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ በይፋ አስታውቋል።

እስካዛሬ በዘለቀው አመጽ ተቃውሞ አድራጊ ዜጎች የፕሬዝዳንቱን መኖሪያ ቤተመንግሥት መቆጣጠራቸው የሚታወስ ነው።

በሙሉጌታ በላይ
2022-07-13