በዓለማችን በርካታ ቀናት ለበርካታ ክዋኔዎች መታሰቢያ ይሆኑ ዘንድ ይከበራሉ። ነገ ደግሞ የአረብኛ ቋንቋ ቀን ተብሎ በመላው ዓለም ይከበራል። ይህ በዓለም ካሉ ቋንቋዎች የበዛ ተናጋሪ አለው የሚባልለት ቋንቋ በየቀኑ ከ4 ሚሊዮን ሰዎች በላይ ለመግባባት ይጠቀሙበታል። ቀኑ እንደፈረንጆቹ የዘመን ቀመር በ2012 ታህሳስ 18 ለመጀመሪያ ግዜ በይፋ ተከብሮ ውሏል። በፈረንጆች የግዜ ስሌት በ1973 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቋንቋውን ስድስተኛ መደበኛ የስራ ቋንቋው አድርጎ የተቀበለው በዚያው በ ታህሳስ 18 ነው። ከፊደላት ቅርፅ፣ ከቃል እስከ ስነግጥማዊ ውበት ድረስ የአረብኛ ቋንቋ እንደ ሥነ ሕንፃ፣ ግጥም፣ ፍልስፍና እና ሙዚቃ ባሉ መስኮች አስደናቂ ውበትን ፈጥሯል። ቋንቋው ለተለያዩ ሀይማኖቶች መዳረሻም እስከ መሆን ደርሷል። በዘመናት ውስጥ የዕውቀት ማስፋፊያ በመሆን ሲያገለግል የነበረው ቋንቋው ከህንድ የባህር ዳርቻ እስከ አፍሪካ ቀንድ ባለው የባህል ሰርጥ ላይ ትልቅ የመግባቢያ ማዕከል በመሆንም አገልግሏል። የዘንድሮው ክብረ በዓልም "የአረብኛ ቋንቋ፣ በስልጣኔዎች መካከል ያለ ድልድይ" በሚል ይከበራል። ቋንቋው የሰው ልጆችን በባህል፣ ሳይንስ፣ ስነ-ጽሁፍ እና ሌሎች በርካታ ዕሴቶች በማስተሳሰር የዋለው ውለታም ይታሰብበታል።
በሀገሬ ቲቪ
2021-12-17
