ሀገሬ ቲቪ

የኤክሳይዝ ታክስ ላይ የግንዛቤ እጥረት መኖሩ ተጠቆመ

ኤክሳይዝ ታክስ የመንግስትን ገቢ ከፍ ለማድረግ ታስቦ የተጣለ እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ :: በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተጀመረው በእንግሊዝ ፓርላሜንት ሲሆን ወቅቱም 1643 ዓ.ም. ነበር ።

ይህ የታክስ አይነት በኢትዮጵያም ከረጅም ጊዜያት በፊት ተግባራዊ የተደረገ ቢሆንም በህዝቡ ዘንድ አስፈላጊው ግንዛቤ ባለመኖሩ የታክስ አፈጻጸም ስርዐቱ በተፈለገው ልክ አለመሄዱን ባለሞያዎች ይናገራሉ።

ይህን ችግር ለመቅረፍ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ኤክሳዝ ታክስን ለሚከፍሉ ነጋዴዎች እናዲሁም ከየክፍለ ከተማው ለተወጣጡ ባለሞያዎች ስልጠና ሰጥቷል ። የኤክሳይስ ታክስን በተመለከተም የግንዛቤ እጥረት እንዳለ በስልጠናው ላይ ተጠቁሟል።

ለመሆኑ ኤክሳይዝ ታክስ ምንድነው ላልናቸው የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ የሆኑት የሆኑት አቶ ዘገየ በላይንህ የቅንጦት ተብለው የተለዩ እቃዎች ላይ የሚጣል የታክስ ዓይነት መሆኑን ገልጸውልናል።

የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ አገር ውስጥ በሚመረቱና ወደ አገር በሚገቡ 19 ዕቃዎች ላይ የተጣለ ሲሆን ከእነዚህ ዕቃዎች ውስጥ ለህብረሰተቡ አስፈላጊ ሆነው ሳለ ቅንጦት ተብለው የተካተቱ እቃዎች በተሻሻለው አዋጅ ከ ኤክሳይዝ ታክስ እንዲወጡ መደረጋቸውን የ አ.አ ገቢዎች ቢሮ የታክስ አማካሪ የሆኑት ወ/ሮ ሰናይት ጸጋየ ይናገራሉ ።

ኤክሳዝ ታክስ የተጣለባቸውን ምርቶችን የሚይዙ ነጋዴዎች ታክሱን በ አግባቡ ካልፈጸሙ ምን በህግ እንደሚጠየቁም ገልጸውልናል።

የኤክሳይዝ ዐላማዎች ታክሱ ከተጣለባቸው ምርቶች ሊሰበሰብ የሚገባው ገቢ በትክክል ተሰብስቦ የአገሪቱን የልማት ዕቅዶች ለማስፈጸሚያ እንዲውል ማድረግ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት እንዲሁም ለጤና ጎጂ የሆኑ ምርቶችን መቀነስ ነው ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-07-14