ሀገሬ ቲቪ

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን መግለጫ

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በአሸባሪነት በተፈረጀው ሸኔ ላይ እየተወሰደ ባለው እርምጃ ቡድኑ መዳከሙን በመግለጫው አስታወቀ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ከበደ ዴሲሳ የሀሰት መረጃዎችን በመልቀቅ እና ለጥፋት ኃይሉ ሽፋን በመስጠት በህዝቦች ዘንድ መጠራጠር እንዲኖር የሚያደርጉ ግለሰቦች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

ሚኒስትር ዲኤታው እንደሚሉት በምዕራብ ወለጋ ጥቃት ለደረሰባቸው ዜጎች መንግስት አስፈላጊውን የሰብአዊ ደጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል።

ከህግ ማስከበር ተግባሩ በተጨማሪ ኃላፊነታቸውን መወጣት ሲገባቸው በመንግስት መዋቅር ስር ሆነው በተለያዩ የሙስና ወንጀሎች የተሳተፉ ባለስልጣናትን ተጠያቂ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

በመቅደስ እንዳለ
2022-07-14