የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭና ከፋይበር ኦፕቲክስ ኪራይ 15 ነጥብ 79 ቢሊዮን ብር አገኘ። በተጠናቀቀው የ2014 በጀት ዓመት ነው የተጠቀሰውን ገቢ ያገኘው።
ከ418 ነጥብ 57 ሚሊዮን ብር በላይ ለኢትዮ- ጅቡቲ ምድር ባቡር ከቀረበ የኃይል ሽያጭ የተገኘ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤለክትሪክ ኃይል አስታውቋል።
በተጨማሪም 94 ሚሊየን ብሩ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያና ዌብስፕሪክስ አይሲቲ ሶሉሽን የተባሉ ኩባንያዎች ከተጠቀመበት የፋይበር ኦፕቲክስ ኪራይ የተገኘ መሆኑ ተገልጿል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-07-14
