የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ያየር ላፒድ ፀረ-ኢራን አቋማቸውን በድጋሜ ለማጠናከር እና ቴህራን የኑክሌር መሣሪያዎችን እንዳታገኝ የሚያደርግ ሥምምነት እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።
በትላንትናው ዕለት የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሒም ራኢሲ ጆ ባይደን በመካከለኛው ምስራቅ እያደረጉት ያለው ጉብኝት በእስራኤል እና በቀጠናው ባሉ ሀገራት መካከል ሰላም የሚያመጣ አይደለም ሲሉ ጉብኝቱን አጣጥለዋል።
ከዚህ ስምምነት ባለፈ አሜሪካ ለእስራኤል የምታደርገውን ወታደራዊ ድጋፍ የምትቀጥልበትን ስምምነት ያደርጋሉ።
በሙሉጌታ በላይ
2022-07-14
