ሀገሬ ቲቪ

በስሪላንካ ተቃውሞ የተጎጂዎች ቁጥር አሻቀበ

በስሪላንካ ወደሳምንት በተጠጋው ተቃውሞ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ 84 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን አልጀዚራ ዘግቧል።

ሟቹ የ26 ዓመት ወጣት ሲሆን ፖሊሶች በተኮሱት አስለቃሽ ጭስ ታፍኖ መሞቱ ተሰምቷል።

የሀገሪቱ የጸጥታ ኃይሎች አስፈላጊውን እርምጃ ወስደው ተቃውሞ አድራጊ ዜጎች የተቆጣጠሩትን መሰረታዊ የመንግሥት ተቋማት እና የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቢሮ እንዲያስለቅቁ ትእዛዝ ተላልፏል።

አሁን ላይ ፖሊሶች ከሰልፈኞች ጋር ጠንካራ ግብግብ ላይ ናቸው። የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ጎታባያ ራጃፓክሳ በትላንትናው ዕለት ከሀገር ኮብልለዋል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-07-14