ሀገሬ ቲቪ

“ዩክሬናውያን መሳሪያ ለሩሲያ እየሸጡ ነው”

በርካታ ሀገራት ፈተናቸው ከዜጎቻቸው ይነሳል። ሰው ለራሱ ያለው ክብር ዝቅ ሲል ከሌለው ከዕለት ጉርሱ ላይ ይነጥቃል። እያወራን ያለነው ስለ ሌብነት ነው፤ በወል መጠሪያው ደግሞ ሙስና።

የዚህ ዓይነቱ ሌብነት በተለይ በአፍሪካ ያሉ ሀገራት ዛሬም ድረስ ዜጎቻቸውን ለአስከፊ ድህነት፤ ሀገራቸውንም ለውድቀት ዳርጓል። እንደው ለነገሩ ለማሳያነት ቀሎን የራሳችንን ጉድ አነሳን እንጂ ችግሩ መላዋን ዓለም የሚፈትን ነው።

ስለ ሌብነት (ሙስና) ይህንን ያልናችሁ የሌብነቱ ጥግ እዚህም ይደርሳል ከማሰኘት አልፎ እጃችንን በግርምት ከአፋችን ላይ ያዋለውን አንድ ተግባር ብንሰማ ነው።

በርግጥ ነገሩ ገና በምርመራ ላይ ያለ ቢሆንም ጉዳዩ አጀብ የሚያስኝ ነው፡፡ እንደ ተባለው ከሆነ አድራጊያኑ ዩክሬናውያኑ ናቸው።ዩክሬናውያን ሀገራቸውን በዓለም ካሉ ሙሰኛ ሀገራት ተርታ ውስጥ አሰፍረዋታል።

እንደምናውቀው ከሩሲያ ጋር በጀመሩት ጦርነት ምዕራባውያኑ ሀገራት ያለ የሌለ መሳሪያቸውን ለዩክሬናውያኑ እያስታቀፏቸው ነው።ታዲያ ምዕራባውያኑ ዩክሬንን ለማጠናክረ በሚል ድጋፋቸውን በተናጠል ብቻም አይደለም፤ በጦር ትስስራቸው ኔቶ በኩልም በርከት አድርገው ለግሰዋታል።

ዩክሬናውያኑ ሀገራቸው እራሷን ነፃ ታወጣበት ዘንድ የተለገሱትን መሳሪያዎች በድብቅ ለሚዋጓት ሩሲያ እየሸጡ ነው እየተባለ ይገኛል። ለሩሲያ ተሽጠዋል ከተባሉት ውስጥ የፈረንሳይ ስሪት የሆነው በመኪና ላይ የሚገጠመው ቄሳር የተሰኘው 155 ሚ.ሜትር የሆነ ከባድ መሳሪያ ይገኝበታል።

መሳሪያው መድፎችን፣ ምሽግ እና ሌሎች የጠላት ከባድ መሳሪያዎችን የማጥፋት አቅም ያለው ነው። መሳሪያው በትክክለኛው ገበያ ላይ ለሽያጭ ቢቀርብ 7 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚያወጣ ይታመንባል።ዩክሬናውያኑ ይህንን መሳሪያ በ120 ሺሕ ዶላር ብቻ ለሞስኮ አሳልፈው ሰጥተዋል ነው የተባለው።

ሀውትዘር የተሰኘው ታንክም ተሽጠዋል ከተባሉት ውስጥ ተጠቅሷል። ቡልጋሪያን ሚሊታሪ ዶት ኮም የተሰኘ ዌብ ሳይት እስንዳሳወቀው ከሆነ ዩክሬናውያኑ በትንሹ የፀረ-ታንክ ሚሳኤል በህገወጡ የበይነ መረብ ክፍል ላይ እስከ 30 ሺሕ ዶላር ሲቸበችቡት ነበር።

በሞደርን ዲፕሎማሲ ላይ የወጣው ፅሁፍ እንደሚያሳያው ከሆነ በራሺያ እና ዩክሬን መካከል ያለው ጦርነት ለዩክሬናውያን ሙሰኞች የተመቸ ሆኖላቸዋል።

የሉቴኒያ የመከላከያ ሚንስትር በሰጠው መግለጫ እስካሁን ለዩክሬ የተደረገው ድጋርፍ ወደ 100 ሚሊዮን ደርሷል።

ተጨማሪ ድጋፍ የማድረግ ፍላጎት ቢኖራትም የዩክሬናውያኑ የሌብነት ነገር ግን እጇን እንድትሰበስብ ሳያደርጋት እንደማይቀር እየተጠቀሰም ይገኛል።

አውሮፓውያኑ ሩሲያን በዩክሬን መሬት ላይ ገጥመዋታል፤ አሁን እንደሚወጡት መረጃዎች ከሆነ ደግሞ የምዕራባውያኑ የጦር ድጋፍ ዞሮ እራሳቸውን ለመውጋት እየውለ ነው።

እነዚህ መረጃዎች ትክክል ሆነው ከተገኙ ነገሮች ወዴት ያመሩ ይሆን ግዜ የሚመልሰው ይሆናል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-07-14