የአብነት ትምህርት የኢትዮጵያ የትምህርት ታሪክ መሠረትና አንድ አካል ሆኖ ቆይቷል፡፡
የአብነት ትምህርት ቤት በልማድ የቆሎ ትምህርት ቤት በመባል በሕዝባችን ዘንድ ይታወቃል።
አንዳንድ ሰዎች ደግሞ የቄስ ትምህርት ቤት አንዳንዶች የቤተ ክህነት ትምህርት ቤት ይሉታል።
የዘመናዊ ትምህርት በሀገራችን መስፋፋቱን ተከትሎ ግን የአብነት ትምህርት ቤቶች ሚና በቤተ ክርስቲያን ብቻ ተወስኖ እንዲቀር ሆኗል፡፡
ከዚያም አልፎ ቤተ ክርስቲያን የነበራትን የመተዳደሪያ ሀብት ንብረት ማጣቷ በአብነት ትምህርት ቤቶች ጥንካሬ ከዚያም አልፎ በህልውናቸው ላይ ፈተኝ ሁኔታዎች ጋርጧል፡፡
ምንም እንኳን ትምሕርቱ አሁን ድረስ በገዳማት እየተሰጠ ቢሆንም የአብነት ተማሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መቷል።
ነቃጥበብ ተስፋ በባሕር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ የአብነት ተማሪ ነው።
ትውልዱና እድገቱ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ደላንታ ነው ።
የአብነት ትምህርቱን ለመከታተል ከ 12 ዓመታት በፊት ወደ ባህርዳር እንደመጣ ይናገራል።
በተለይም ከኅብረተሰቡ ምግብ ለማግኘት እንቸገራለን፤ እኛ ግን አግለግሎቱ ላይ ነው የምናተኩረው ይላል
የቅኔ የትምህርቱ ቆይታን በተመለከተ ተማሪው ሲያብራራ
ወላጆቹ ወደ አብነት ትምህርት በመግባቱ ቅር እንደተሰኙበትም ነግሮናል።
ከተማ ቀመስ ለሆነ ሰው የአብነት ትምህርት ከባድ ነው ባይ ነው ነቃጥበብ
በቀጣይ የአብነት ተማሪው ነቃጥበብ የድጓ መምህር የመሆን ህልም አለው። ህልሙንም እውን ሊያደርግ ዘወትር ይተጋል።
በማኅበረ ቅዱሳን በቅዱሳት መካናትና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የገቢ አሰባሰብና መረጃ ማጠናቀሪያ ዋና ክፍል ምክትል ሀላፊ ዲያቆን ሰሎሞን ወልዴ የአብነት ትምህርት ቤቶች፣ መምህራን ፣ ተማሪዎች የመቀነሳቸውን ምክንያት ሲያስረዱ
ምዕመኑ ለአብነት ተማሪዎች ከዚህ በፊት ሲያደርግ የነበረውን ትኩረትና ድጋፍ መቀነሱ ሌላኛው ችግር ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
በቀጣይም መምህራኑንም ተማሪዎቹንም እንደግፋለን ሲሉ ዲያቆን ሰለሞን ይናገራሉ።
አባ ጊዮሪጊስ ዘጋስጫ የተሰኘ ነጻ የትምህርት እድል ተመቻችቷል ተብሏል።
የትምህርት መረሃግብሩ የአብነት ትምህርትን ያስፋፋል ተብሎ ተስፋ ተጠሎበታል ። መርሃ ግብሩም በመላው ኢትዮጵያ በተመረጡ ክልሎች ተግባራዊ ለማድረግ ማኅበረ ቅዱሳን አቅዷል።
በአብነት ትምህርት የፊደልና የንባብ ፣ የቋንቋ ፣ የዜማ ፣ የቅኔ ፣ የትርጓሜ ና የቁጥር ትምህርቶ ይሰጣሉ።
በአሁኑ ጊዜ ከ 5000 በላይ የአብነት መምህራንና ከ 100,000 በላይ የአብነት ተማሪዎች እንዳሉ ይገመታል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-07-18
