ደቡብ አፍሪካ በምትዋሰነው የህንድ ውቂያኖስ የመርዛማ ኬሚካል ማስወገጃ ሆኗል ተባለ፡፡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በሐምሌ 2021 በሰሜን ደርባን በኮርኒቢያ በሚገኘው የኬሚካል ማከማቻ መጋዘን ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ምክንያት የተባይ ማጥፊያ እና ሌሎች አግሮ ኬሚካሎች ወደ ባህር ውስጥ ሊፈስ ችሏል፡፡ መርዛማው ኬሚካል ወደ ውቂያኖሱ ከፈሰሰ በኋላ የአካባቢው ነዋሪዎች የጤና መታወክ እንደደረሰባቸው ተነግረዋል፡፡ ለደህንነት ጥበቃ ሲባልም በርካታ የከተማዋ ታዋቂ የመዋኛ የባህር ዳርቻዎች ለአራት ወራት ያህል እንዲዘጉ ተደርጎ ነበር፡፡ ሰዎች የሚዝናኑበት የባህር ዳርቻ ለአገልግሎት ክፍት ከሆነ ከአንድ ወር በኋላ ታዲያ ዩናይትድ ፎስፈረስ የተባለ የኬሚካል አምራች ድርጅት የተለያዩ መርዛማ ኬሚካሎችን ወደ ውቂያኖሱ ሊያስወግድ አቅዷል ሲል ኦልአፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡ የደቡብ አፍሪካ የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተቋሙ ውቂያኖሱን ከመበከል እንዲቆጠብ የተቃውሞ ድምጻቸውን እያሰሙ ይገኛሉ፡፡
በሀገሬ ቲቪ
2021-12-17
