በስሪላንካ በተከሰተው የምጣኔሀብት ቀውስ ምክንያት ሳምንት በተሻገረው ሕዝባዊ አመጽ ፕሬዝዳንት ራጃፓክሳ ስልጣናቸውን ጥለው ከሀገር መኮብለላቸው አይዘነጋም መጀመሪያ ወደጎረቤት ሀገር ማልዲቭስ በስተመጨረሻም ወደ ሲንጋፖር አቅንተዋል።
የሳቸን ከሀገር መሸሽ ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ራኒል ዊከርምሲንጌ ጊዜአዊ ፕሬዝዳንት ለመኾን ባላፈው ሳምንት ቃለመሀላ ፈጽመዋል።
ይህን ጊዜአዊ ስልጣናቸውን በሀገሪቱ አስቸኳይ አዋጅ በማወጅ ጀምረውታል። ዊከርምሲንጌ በጉዳዩ ላይ ባደረጉት ንግግር። የስካሁኑ ግርግረ እና ረብሻ ይበቃል አሁን ወደቀልባችን እንመለስ ብለዋል። ከዚህ በኋል የሕዝብን ድኀንነት እና ሥርዓት ማስጠበቅ ይገባናል ሲሉ ተነግረዋል።
የአስቸኳይ አዋጁ መታወጅ የተቋረጡ አገልግሎት እንዲጀመሩ የወደሙ ንብረቶች እንዲታደሱ ሥጋት ውስጥ የወደቀው የሕዝብ ድኀንነት እንዲመለስ እንደሚረዳ የቀድሞ የሲሪላንካ ጠቅላይሚኒስትር የአሁኑ ጊዜአዊ ፕሬዝዳንት ራኒል ዊከርምሲንጌ።
በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተወሰኑ ሕጋዊ ድንጋጌዎች ገና በመንግሥት ይፋ ባይሆኑም ቀደም ሲል የወጡ የአስቸኳይ ጊዜ ደንቦች የጸጥታ ኃይሎች ተጠርጣሪዎችን ለማሰርና ለመያዝ፣ በግለሰብ ንብረቶች ላይ አስፈላጊውን ፍተሻ ለማድረግ እና ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን ለማብረድ ጥቅም ላይ መዋላቸው አልጀዚራ በዘገባው አስታውሷል።
አስቸኳይ አዋጅ ማወጅ ያን ያህል ለውጥ ሊያመጣ የሚችል አይደለም ከንቱ እርምጃ ነው ያሉ ፖለቲክርኞች አልጠፉም። አስቸኳይ አዋጅ የመንግሥትን ግብታዊ እርምጃ የሚያሳይ ነው ብለውታል።
ጊዜአዊው መንግሥት ግን በነዳጅ ውድነት፣ ለሕዝቡ አልቀመስ ባለው የሸቀጦች ዋጋ መቸገሩን አረጋጋለሁ በእኔይኹንባችሁ ሲል ቃል ገብቷል።
በነዳጅ እጥረት ሲሰቃይ ለቆየው ሕዝብ እፎይታ ለመስጠትም ነዳጅ ወደሲሪላንካ እየገባ ነው ተብሏል።
አሁን ላይ ሲሪንካ ቀጣይ አምስት ዓመታትን የሚመራትን መንግግስት ለመምረጥ ሽርጉድ ላይ መኾኗም ተሰምቷል። ይህንን ጉዳይ ከግብ ለማድረስም ፓርላማው ከቅዳሜ ዕለት ውይይቱን ጀምሯል።
ሲሪላንካ ከሚያዛ ጀምሮ አስቸኳይ አዋጅን በተደጋጋሚ ስታውጅ ቆይታለች። የሲሪላንካ ዋና ከተማ ኮሎምቦ የዛሬ ውሎዋ የተረጋጋ ሕዝቡም ወደቀድሞ የሥራ ደፋቀናው እንደተመለሰ መረጃዎች ጠቁመዋል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-07-18
