ሀገሬ ቲቪ

ከንቲባው ማስፈራራት ጀምረዋል

በፊሊፒንስ ውስጥ የምትገኝ የአንድ ከተማ ከንቲባ ለመንግስት ሰራተኞች ካሁን በኋላ አንድ ህግ አውጥቻለሁ መፈጸምም ግዴታ ነው ብለዋል ።

ከንቲባው ያውጡት ህግ እንዲህ የሚል ነው። ካሁን በኋላ በ እኔ ግዛት ያላቹ የመንግስት ሰራተኞች እና ባለስልጣናት ማንኛውም ህዝብ ለመገልገል ወደናንተ ሲመጣ ፈገግ ማለት ውዴታቸሁ ሳይሆን ግዴታቹ ነው። ምክንያቱም ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ በስራ ገበታው ላይ የተቀመጠው ህዝብን ለማገልገል ነው።

በየወሩ የሚከፈለው ደሞዝም ከህዝብ ኪስ የተሰበሰበ ነውና ። መመሪያውን አላከብርም ላላቹ ከስራ ገበታቹ ላይ ከማገድ በተጨማሪ የዲሲፕሊን እርምጃ እወስዳልሁ ሲሉ ዝተዋል።

ከንቲባ አሪስቶትል አጉዌራ የሙላናይ ማዘጋጃ ቤት ከንቲባ ሲሆኑ ይህ "የፈገግታ መመሪያ" በሠራተኞች መካከል ያለውን ደካማ መንፈስ ለማሻሻል እንዲሁም ማንኛውም ተገልጋይ ለ ሰራተኞቻችን በጎ አመለካከት እንዲኖረው ያስችላል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ፖሊሲው ከአስተዳደሩ ዋና ዋና መርሃ ግብሮች አንዱ እንደሚሆን ትዕዛዙ ላይ የተመላከተ ሲሆን "የመረጋጋት ስሜት እና ወዳጃዊ ሁኔታን በማሳየት ቅንነትን ያሰፍናል" ብለዋል ።

ከንቲባው እርሶ ያዘዙት ትዕዛዝ በየ መስሪያ ቤቱ መተግበሩን በምን ያረጋግጣሉ ሲባሉም ። በማንኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት ይህን ሊቆጣጠር የሚችል የሰው ሃይል እንዲሁም የካሜራ እይታ እንዘረጋለን። ይህ በፍጹም ልንሽረውም የማንችለው ህጋችን ነው ብለዋል ።

በሀገራችን ኢትዮጵያ በህዝብ አገልጋዮችና በተገልጋዮች መካከል ከፍተኛ ቅሬታ ሲነሳ ይስተዋላል ። አሁን አልችልም ፤ ስብሰባ ላይ ነን ፤ እርሳቸውን ማግኘት አይችሉም የሚሉ ንግግሮች በብዙ የህዝብ አገልጋዮች ዘንድ የሚስተዋሉ ሲሆን ይህ ተግባር ብዙዎችን ለመንግስት ሰራተኞች ጥሩ አመለካከት እንዳይኖራቸው አድርግዋል ።

ይህ በፊሊፒንስ የወጣው ህግም የከተማውን ህዝብ በ እጅጉ ያስደሰተ ሲሆን ። ለሌሎች ሀገራትም ከዚህ እንዲማሩ በር ከፋች ነው ።

በዮሴፍ ከበደ
2022-07-18