የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ጉብኝታቸው ግብጽን አካቷል።
የሁለቱ ሀገራት ፕሬዚዳንቶች የኢትዮጵያን ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
አል ሲሲ ሀገራቸው የግድቡን የውሃ ሙሌትና ቀጣይ ሥራ በተመለከተ የግብፅን የውሃ ዋስትና በሚያስከብር ሁኔታ አሳሪ ሕጋዊ ስምምነት እንዲደርስ ያላትን ጽኑ አቋም ለባይደን ገልፀዋል።
ባይደንም አሜሪካ የግብፅን የውሃ ዋስትና እንደምትደግፍ እና ለአካባቢው ሰላም አስተዋጽኦ የሚያደርግ፣ የሁሉን ወገኖች ጥቅም የሚያስከብር ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ላይ እንዲደረስ ጠይቀዋል።
በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-07-18
