በደቡብ አውሮፓ ሀገራት በተነሳው ሰደድ እሳት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺሕ አለፈ።
ይህ ዘገባ እሰከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ስፔን፣ ፖርቹጋል፣ ጣልያን፣ ክሮኤሺያ፣ ግሪክ እና ፈረንሳይ የሰደድ እሳቱ ሰለባ ሆነዋል።
ፈረንሳይ በደቡብ ምዕራብ በሰደድ እሳት ስጋት ላይ የወደቁ ከ16 ሺሕ የሚበልጡ ሰዎችን ከአካባቢው አስወጥታለች።
በምዕራብ ከሞሮኮ አንስቶ በስተ ምሥራቅ እስከ ቀርጤስ በሜድትራንያን ባሕር ማዶ ድረስ የተስፋፋውን እሳት ለማጥፋት በሺሕ የሚቆጠሩ የእሳት አደጋ ሠራተኞችና አውሮፕላኖች ተልከዋል ።
በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-07-18
