ሀገሬ ቲቪ

‘‘400 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዷል’’ ግብርና ሚኒስቴር

በያዝነው የምርት ዘመን 400 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዶ የቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ። ይህንን የተናገሩት የግብርና ሚኒስቴር የእርሻና የሆልቲካልቸር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር መለስ መኮንን ናቸው።

በምርት ዓመቱ 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ስለመታረሱም ሚኒስትር ዲኤታው ገልጸዋል። ለማቅረብ ከታሰበው ከ15 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ 8 ሚሊዮን ያሀሉ ብቻ ለአርሶ አደሩ መቅረቡንም ተናግረዋል። 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በትራክተር ለማረስ ታቅዶም 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር መታረሱንም ገልጸዋል።

በአብርሃም በለጠ
2022-07-19